Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ስለ እኛ ራዕይ

ሚዲያ በደረስንበት የቴክኖሎጂ ዘመን አጥፊም አልሚም መሆን እንደሚችል ተመልክተናል ። በተለይ ሚዲያን ለልማት በማዋል ከፍተኛ ሀገራዊ ጥቅም ያካባቱ ሀገራት ቁጥራቸው የትየለሌ ነው። በዛው ልክ ደግሞ ሚዲያን ላልተገባ አላማ፣ ህዝብን ከህዝብ ለመለያየት፣ ለጥላቻ ንግግር የሚጠቀሙ ባለባቸው ሀገራት በችግር ላይ ችግር እየደራረቡ ልማት ናፋቂ ከመሆን አልፈው እንደሀገር የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸው ሀገራትም ሞልተዋል ።

ያለንበት የዲጂታል አለም በየእለቱ በርካታ ኩነቶችን የምታስተናግድበትን ሁኔታ ሚዲያው በየማይክሮ ሰከንዱ ወደ አድማጭ ተመልካች እያደረሰ አለም አንድ መንደር መሆኗን በተጨባጭ እያሳየ በሚገኝበት በዚህ ዘመን ሚዲያ የማይተካ ሚና ሲጫወት ይታያል ።

እንደ ሀገራችን የሚዲያ እንቅስቃሴም በተመሳሳይ በመንግስት የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች እና በየእለቱ የሚከሰቱ ኩነቶችን በመከታተል ለህዝብ የሚያደርሰው ሚዲያ በሀገራችን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፍ ትልቅ አወንታዊም አሉታዊ ተፅእኖ በመፍጠር ላይ ይገኛል ። የቀቤና ልዩ ወረዳ የሚዲያ እንቅስቃሴ ገና ዳዴ እያለ ያለ ቢሆንም በልዩ ወረዳው የሚሰሩ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ህዝብ እንዲያውቃቸው ከማድረግ በተጨማሪም ህዝብና መንግስትን ለማገናኘት እንደ አይነተኛ መሳሪያ ያገለግላል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት በልዩ ወረዳው የሚከናወኑ የልማት ፣የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ለይቶ አፈፃፀማቸውን እግር በእግር እየተከታተለ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለህዝብ እንዲደርሱ ያደርጋል። በተጨማሪም የባህል፣ቋንቋ፣ታሪክ ፣እሴቱ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ልዩ ወረዳው ለልማት ያለውን ከፍተኛ አቅም ለሌላው አለም ለማስተዋወቅ ይሰራል ።