የቀቤና ልዩ ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ።
08 Jul 2026

(ወልቂጤ፣ ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም) የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ፈጻሚ ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል ።
የልዩ ወረዳው የፕላንና ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዛኪር አብድልሀይ የየተቋማቱን የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት ለመድረኩ አቅርበዋል።
በሪፖርቱ ላይ እንደተመለከተው በበጀት ዓመቱ በዕቅድ የተያዙ የልማት ግቦች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹም በቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በተለይም ህዝብን በማስተባበር በራስ አቅም የኢማም ሀሰን ኡንጀሞ ሆስፒታል እና የፈትሁዲን አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመር መቻሉ፣በርካታ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ማስመረቅ መቻሉ፣ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተማሪዎች ምገባ ከማስጀመር በዘለለ የትምህርት ቤት ጥገናና ግምባታ መከናወኑ ተገልጿል ።
በግብርናው ዘርፍ ልዩ ወረዳው የሚታወቅበት የበልግና እና የመኸር የግብርና ስራዎችን አጠናክሮ በመያዝ በመስኖና በፀደይ እርሻ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ የዘለለና ለክልሉ ተሞክሮ የሚሆን ተግባራት መከናወናቸው ተጠቁሟል ።
በጤናው ዘርፍ የፅዱ መንደር ፅዱ ቀበሌን ጨምሮ ፣ የጤና ጣብያ አገልግሎት አሰጣጥ ከማሻሻል ፣ የመድኃኒት አቅርቦት፣ በማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ማህበረሰቡን ከማስጠቀም አኳያ አበረታች ውጤቶች ተመዝግቧል ።
የገቢ አቅምን በማሳደግ በልዩ ወረዳው የቢሮ ግንባታን ጨምሮ በርካታ ግንባታዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን በመንገድ ልማት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከፈታና ጠረጋ፣ የወሸርቤ ጣጤሳ የቦቶ ድልድይና የደቀንሺሞላ ተንጠልጣይ ድልድይ መሰራቱንና በዚህም ለረዥም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው የቆዩ የማህበረሰብ ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት መቻላቸው ተጠቅሷል ።
በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በርካታ የልዩ ወረዳው ማህበረሰብ ስልጠናውን እንዲወስዱ መደረጉ የተገለፀ ሲሆን በዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ።
በሰራ እድል ፈጠራ በበጀት አመቱ አዳዲስና ነባር የስራ እድል ከመፍጠርና የተፈጠረላቸውን ከማጠናከር አኳያ አበረታች ስራዎች መሰራታቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም አጠናክሮ ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቅሷል ።
ከሰላም ግምባታ አኳያ የሁሉም ነገር መሠረቱ ሰላም በመሆኑ በተለይ የቀጠናውን ሰላም አስጠብቆ ለመሄድ ከተለያዩ የፀጥታ ባለድርሻ አካላት በጋራ በመስራት እና ማህበረሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የተሻለ የሰላም እንቅስቃሴ እንዲኖር ማድረግ መቻሉ ተገልጿል ።
በአጠቃላይ በልዩ ወረዳው በሁሉም ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውንዠ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ በ2019 የበጀት አመት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተጠቁሟል ።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድአሚን በደዊ ባደረጉት ንግግር፤ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት በልዩ ወረዳው በሁሉም ዘርፎች ውጤታማና አበረታች የሆኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም፣ በበጀት ዓመቱ ለመፈጸም የታቀዱ ተግባራት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በጥልቀት መገምገም እንደሚገባ ጠቁመው፤ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ጉድለቶችንና ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም በቀጣይ እቅድ አካክሶ ለመፈፀም ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ የሕዝቡን የልማትና የደኅንነት ጥያቄዎች በበለጠ ፍጥነትና ጥራት ለመመለስ፣ የሁሉም ፈጻሚ አካላት የተቀናጀ ጥረትና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨማሪ ምስሎች