የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎችን በልዩ ትኩረት በመፈጸም የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አመራሩ የአመራርነት ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።
29 Oct 2025

(ወልቂጤ፤ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ) የቀቤና ልዩ ወረዳ አዲሱ አስተባባሪ በልዩ ወረዳው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ለማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከልዩ ወረዳው አመራሮች ጋር በመወያየት የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል ።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ በመድረኩ እንደተናገሩት ልዩ ወረዳው በ2017 የተግባር አፈፃፀም በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ እንደነበር አስታውሰው ይሄንን በ2018 በጀት አመትም በተሻለ መልኩ ለመፈፀም በየደረጃው የሚገኘው አመራር በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
አክለውም አመራሩ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎችን በልዩ ትኩረት በመፈጸም የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የአመራርነት ሚና መሆኑን ገልፀው አመራሩ ሚናውን በተገቢው አውቆ የተጠናከረ ስራ በመስራት የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ብለዋል።
በተመሳሳይም የቀቤና ልዩ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ካፉ አረቦ እንደገለፁት የሰላም ግንባታ ስራዎችን በማጠናከርና የገቢ አቅምን አሟጦ በመጠቀም በልዩ ወረዳው የታለሙ የልማት እቅዶችን ለማሳካት መትጋት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
አክለውም የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በፓርቲ ቅኝትና በአደረጃጀት በመፈጸም የተጀማመሩ የሰላም፣የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የልዩ ወረዳው አመራሮች በሰጡት አስተያየትም ለሰላም፣ ለልማትና ለተቋም ግንባታ የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት በትኩረት እንደሚሰሩ በመግለፅ አዲሱ አስተባባሪ በየደረጃው የሚከናወኑ ሁለንተናዊ ተግባራትን እግር በእግር መከታተልና መደገፍ ይገባዋል ብለዋል።
አክለውም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በየደረጃው ከሚገኙ አካላት ጋር ውይይቶችን በማድረግ ለተግባር ምቹ ምህዳር መፍጠር እንደሚገባ አመላክተዋል ።
መድረኩ በቀጣይ የተግባር አፈፃፀም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችሉ የስራ አቅጣጫዎችን በማመላከት የተጠናቀቀ ሲሆን በውይይቱ የልዩ ወረዳው አስተባባሪ አካላትን ጨምሮ መላው አመራር ተገኝቷል ።
*****