Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት መሆኑ ተገለፀ ።

27 Oct 2025
የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት መሆኑ ተገለፀ ።

የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት መሆኑ ተገለፀ ።

27 Oct 2025

የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት መሆኑ ተገለፀ ።

(ወልቂጤ ጥቅምት ፣17/2018 ዓ.ም ) በቀቤና ልዩ ወረዳ "የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት ነው" በሚል መሪ ቃል የ2ኛ ዙር የሴቶች የልማት ህብረት ሞዴል ቀበሌ የመፍጠር የማጠቃለያና የ3ኛ ዙር የሞዴል ቀበሌ ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄዷል ።

በመድረኩ የተገኙት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ዙልፋ አለዊ በመድረኩ እንደተናገሩት በፓርቲያችን ብልፅግና ኢኒሼቲቭ በሴቶች የልማት ህብረት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

አክለውም በልዩ ወረዳው ከ1ኛ እስከ 2ኛ ዙር በሴቶች የልማት ህብረት በሞዴልነት በተመረቁ ቀበሌዎች የሚገኙ ሴቶች እቅዶቻቸውን የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀትን ተጠቅመው በመምራታቸው ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ መቻላቸውን ጠቁመዋል ።

በተመሳሳይም እንደሀገር ሴቶች ሁሉንም ማድረግ እንደሚችሉና በልዩ ወረዳውም የሚሰፉ ምርጥ ተሞክሮች እንዳሉ ማየት መቻሉን ገልፀው በቀጣይ በ3ኛው ዙር የሴቶች የልማት ህብረት የሞደል ቀበሌ መፍጠር መርሀ ግብር ይሄንኑ አስጠብቆ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በተጨማሪም ሴቶች ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ የኢኮኖሚ አቅማቸውን የሚያሳድግ ስራ መስራትና የቁጠባ ባህላቸውን በማጎልበት ከኢኮኖሚ ጥገኝነት መላቀቅና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የራሳቸውን አሻራ ማኖር እንደሚገባቸው ገልፀዋል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲሀ ሱልጣን እንዳሉት ባለፈው የ2ኛ ዙር የሴቶች የልማት ህብረት ሞዴል ቀበሌዎችን የማስመረቅ ሂደት ውስጥ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቁመው በቀጣይም በልዩ ወረዳው 3 ቀበሌዎች ማለትም :- ፈረጀቴ፣ ሌንጫና ቆላ ቀበሌዎች በ3ኛ ዙር በሴቶች የልማት ህብረት ሞዴልነት ይመረቃሉ ብለዋል።

በዚህም በየደረጃው ያለው የሴቶች የልማት ህብረት ስትሪንግ ኮሚቴና ባለድርሻ አካላት ተግባሩ ቀጣይነት እንዲኖረው ከማድረግም በላይ ሞዴል ተደርገው የተመረቁ ቀበሌዎች ሞዴልነታቸውን አስጠብቀው እንዲሄዱና ባህል ሆኖ እንዲቀጥል ሊያግዙ ይገባል ብለዋል።

''አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ'' አይሆንም ያሉት ኃላፊዋ በሴቶች የልማት ህብረት በትምህርት ፣በጤና፣ በግብርና ፣በስራ እድል ፈጠራና በሌሎችም ተግባራት ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤታማ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ ገልፀው ለዚህም ቅንጅታዊ አሰራሮችን መከተል ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ በሴቶች የልማት ህብረት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት መነሻነት ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ።

በተለይም በልዩ ወረዳው የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀቶችን ከማጠናከር ፣ ግንዛቤ ከመፍጠርና ከቅንጅታዊ አሰራሮች ጋር ያሉ ውስንነቶችን በቀጣይ እያረሙ መሄድ እንደሚገባ ተመላክቷል ።

በልዩ ወረዳው ያልታዩና ያልተሰራባቸው በርካታ እምቅ የመልማት አቅሞች መኖራቸው በተገለፀበት በዚህ መድረክ ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ እያበቁ መሄድ ከተቻለ
ያሉ አቅሞችን አሟጦ የመጠቀም እድል መፍጠር እንደሚቻል በመድረኩ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በልዩ ወረዳው በፍቃዶ ቀበሌ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሴቶች የልማት ህብረት እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት ስራዎችና የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራች የልማት ህብረቶች ተግባር ዙሪያ ምልከታ በማድረግና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተመልክቷል ።

በመጨረሻም በሴቶች የልማት ህብረት ተግባር የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት፣መዋቅሮችና ለሞዴል የሴቶች የልማት ህብረት አባል እናቶች የእውቅና ሰርተፍኬት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

ተጨማሪ ምስሎች