Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት " የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

26 Oct 2025
የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት " የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት " የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

26 Oct 2025

የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት " የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

ወልቂጤ፣ ጥቅምት 16/2018 ዓ.ም

የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ሪፖርት፣ የ2018 ዋና ዋና ግቦች እና የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ማካሄዱን ገለፀ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ፈቱዲን ሙዘሚል ልዩ ወረዳው በበቆሎና የጤፍ ሰብል ምርታማነትና የክላስተር እርሻ እንደ ሀገር እየታወቀ መምጣቱን ገልፀው ይሄን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም በሌሎችም የፍራፍሬ፣ የቡና እና የቅመማ ቅመም ምርቶች ላይ የልዩ ወረዳው ብራንድ ለማድረግ መስራት ይገባል ብለው በተመሳሳይም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አርሶ አደሩ ፈጥኖ እንዲተዋወቅ ከማድረግ አንፃር ባለሙያዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የባህርዛፍን በማስወገድ ቦታውን በፍራፍሬና በሰብል እህል እንዲሸፈን ለማድረግ የቀበሌ አመራሮች ከአርሶ አደሩ ጋር በመነጋገር ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልሽኩር ደሊል በ2017 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ወደ ተግባር መገባቱን አስታውሰው በዚህም በግብርናው ዘርፍ አበረታች ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል ።

እቅዱን ለማሳካት የተቀናጀ የግብርና ንቅናቄ መድረክ ከመፍጠረ ባሻገር ለልማት ጣቢያ ሰራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት ወደ ተግባር በመገባቱ ውጤታማ መሆን እንደተቻለም ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ በበጋ መስኖ እርሻ አበረታችና ውጤታማ ስራ በመሰራቱ ከፍተኛ ምርት ማምረት መቻሉንም አንስተዋል ።

አክለውም ግብርና የሀገራችን የኢኮኖሚ ዋልታ መሆኑን ጠቅሰው የአርሶ አደሩን አኗኗር ለማሻሻል እና የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ እንደ ቀቤና ልዩ ወረዳ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ጥራት ያለው እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል።

የቡናና ቅመማ ቅመም ልማትና ግብይት ስራዎችንና የቡና ችግኝ ዝግጅትና የማሳ ሽፋን ለማሳደግ ሰፊ ስራ በመሰራቱ እንደ ሀገር ኤክስፖርት የሚደረጉ ምርቶች ላይ አስተዋፅኦ ማበርከት መቻሉንም ገልፀዋል ።

በመድረኩ የእንስሳት ምርታማነት ለማሳደግና የእንስሳትን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል በርካታ ተግባራት መከናወናቸው የተገለፀ ሲሆን በዚህም የዳልጋ ከብት በማዳቀል ዝርያ የማሻሻል፣ የመኖ እፅዋት አቅርቦት፣ የአንድ ቀን ጫጩት አቅርቦት፣ በንብ እርባት ወጣቶችን በማደራጀትና ወደ ስራ በማስገባት ሰፋፊ ሥራዎች መሠራታቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይም ዘላቂ የተፈጥሮ ሀብት ልማትና አጠቃቀም ስራዎች በተመለከተ የተፋሰስ ስራዎች የጥናትና የዲዛይን ሥራ በመስራት አመርቂ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን፣ የአረንጓዴ አሻራ አፈፃፀም ለማሳደግ የችግኝ ጣቢያዎችን በዓይነትና በባለቤትነት ለይቶ ወደ ስራ በማስገባት ከ6. 2 ሚሊየን በላይ ችግኝ መትከል እንደተቻለም ተነስቷል።

በበጀት ዓመቱ 15 የግብርና ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ በፍራፍሬ፣ በዶሮ ልማት፣ በተሻሻለ የዳልጋ ከብት ዝርያ እና በሌሎችም ኣኒሼቲቮች አበረታች ውጤት መመዝገቡን በሪፖርቱ በዝርዝር ተመላክቷል።

እንደ አጠቃላይ በ2017 በጀት ዓመት በአምስት የምርት ወቅቶች ከ34 ሺህ 6 መቶ 38 ሄክታር መሬት በላይ በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑም ተገልጿል።

በ2018 በጀት ዓመት የበጋ የመስኖ የተቀናጀ ግብርና ልማት ተፈፃሚ ለማድረግ 12 ግቦች በመቅረፅ እስከ ታችኛው መዋቅር የንቅናቄ መድረክ የሚፈጠር መሆኑን የተገለፀ ሲሆን፣ በ2018 በበጋ መስኖ የተቀናጀ ግብርና ልማት 8 ሺህ 836 ሄክታር መሬት የማልማት ሥራ እንደሚሰራ ተጠቁሞ 2ሚ 2 መቶ ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተገልጿል።

እቅዱን ተፈፃሚ ለማድረግም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀና የተጠናከረ እርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው የተገለፀ ሲሆን የጉባኤው ተሳታፊዎች በቀረበው ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት ግቦች ላይ ላነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አብድሽኩር ደሊልና የተቋሙ የማኔጅመንት አካላት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ምስሎች