Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

ዋና ገጽ ዜናዎች አገልግሎቶች ስለ እኛ አግኙን
ወደ ዜናዎች ተመለስ

የወባ በሽታ መከላከል ቅድመ ማስጠንቀቂያ!

24 Oct 2025
የወባ በሽታ መከላከል ቅድመ ማስጠንቀቂያ!

የወባ በሽታ መከላከል ቅድመ ማስጠንቀቂያ!

24 Oct 2025

የክረምቱ ወቅት አልፎ የበጋው ወቅት መተካቱን ተከትሎ በሚፈጠር ሙቀትና ውሃ በሚያቁሩ ኩሬዎች ምክንያት የወባ ትንኝ ከወትሮው በተለየ መልኩ ሊራባ ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ።

በመሆኑም የወባ በሽታን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው
*****************************

👉አጎበርን በአግባቡ መወጠር
👉አጎበርን ሁሌም በአግባቡ መጠቀም
👉በፀረ-ወባ ኬሚካል በተነከረ አጎበር ውስጥ መተኛት
👉የአጎበር አጠቃቀም ላይ ለነፍሰጡር እናቶችና ለህጻናት ቅድሚያ መስጠት
👉አጎበርን ለታለመለት አላማ በማዋልና መጠቀም
👉የቤት ውስጥ የፀረ ወባ ትንኝ ኬሚካል ቤትዎን ማስረጨት
👉በጸረ-ወባ ኬሚካል የተረጨ ግድግዳ ላይ እስከ 6 ወር ቀለም አለመቀባት፤ እበት ባለመለቅለቅ፤ በወረቀት አለመሸፈን
👉በግቢዎና በአካባቢዎ ያሉ ዉሃ የሚያቆሩ ቦታዎችንና ቁሳቁሶችን እንደ መኪና ጎማ፣ የሸክላ ስባሪዎች፣ የወዳደቁ ጣሳዎች ማስወገድ፡ ማፋሰስ፤ መደልደል

👉እንደ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማንቀጥቀጥ ምልክት ካጋጠመ በወባ በሽታ ተይዘው ሊሆን ስለሚችል ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም መሄድና ህክምና ማድረግ
👉በምርመራ የወባ በሽታ መሆኑ ከተረጋግጠ በጤና ባላሙያ በታዘዘሎት መሰረት መድኃኒቱን ጨርሶ መውሰድ
👉በወባማ አካባቢዎች ከአንድ ወር በላይ ቆይተው ሲመለሱ የወባ በሽታ ምርመራ በማድረግ ራስዎን ቤተሰቦን እና ማህበረሰቡን ከወባ በሽታ ይከላከሉ፣"

የተከለከሉ ጉዳዮች
***********

👉የወባን በሽታ እራስን በራስ ማከም የተከለከለ ነው
👉የወባ በሽታ ምርመራ ሳያደርጉ የወባ በሽታ መሆኑን ሳያውቁ መድሃኒት መውሰድ ፍጹም የተከለከለ ነው
👉ለአንድ ሰው የታዘዘን መድሃኒት ለሌላ ማካፈል የተከለከለ ነው
👉በጤና ባላሙያ የታዘዘሎትን የወባ መድኃኒት ጨርሰው አለመዉሰድ በሌላ ጊዜ በመድሃኒቱ እንዳይፈወሱ ያደርጋል

👉ከመድሃኒት ውጤታማነትና በአወሳሰድ ስህተት የሚፈጠሩ ችግሮች ካሉ ወዲያውኑ ወደ ሃኪም ቤት እንዲሄዱ ይመከራል።

******
የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት